ማቴዎስ 10:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋን ከመግደል አልፈው ነፍስን መግደል የማይችሉትን ሰዎች አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን አምላክ ፍሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋን መግደል እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ማጥፋት የሚቻለውን ፍሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን እርሱን ፍሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ፤ ታዲያ እንደ ሣር የሚጠወልገውንና መሞት ያለበትን ሰውን የምትፈሩት ለምንድን ነው?
እነዚህን ሁሉ ነገሮች የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ ስለዚህ ሁሉም የእኔ ናቸው፤ እኔ የምመለከተው ልባቸው ወደ ተሰበረ፥ ትሑት መንፈስ ወዳላቸውና፥ ቃሌንም ወደሚያከብሩ ነው።
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።
ጳውሎስ ግን “እንደዚህ እያለቀሳችሁ ስለምን ልቤን በሐዘን ትሰብሩታላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ።
ሴቶች የሞቱባቸውን ዘመዶቻቸውን ከሞት ተነሥተው አገኘአቸው። ሌሎችም የበለጠ ትንሣኤ ለማግኘት አስበው ልዩ ልዩ ሥቃይ ተቀበሉ፤ ከእስራት ነጻ መሆንንም አልፈቀዱም።
ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ሊያድንም ሊያጠፋም የሚችል እርሱ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ በሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።