ማቴዎስ 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ሰዎች ቅጣቱ ይቀልላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነት እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ቅጣቱ ይቀልላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነት እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነት እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል። |
በፍርድ ቀን ብዙዎች፥ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።
ሰዎች በማይቀበሉአችሁና በማይሰሙአችሁ ቦታ ሁሉ የእግራችሁን አቧራ አራግፉና ከዚያ ወጥታችሁ ሂዱ፤ ይህም ለእነርሱ የማስጠንቀቂያ ምስክር ይሆንባቸዋል።”
አዎ! የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያይና በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።”
እርሱ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ሁሉ ላይ በእውነት የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአል፤ ይህንንም ለሁሉም ያረጋገጠው ያን የመረጠውን ሰው ከሞት በማስነሣቱ ነው።”
የእያንዳንዱ ሰው ሥራ የሚገለጥበት የፍርድ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ቀን የእያንዳንዱ ሰው ሥራ ምን ዐይነት እንደ ሆነ በእሳት ተፈትኖ ይገለጣል።
ዘወትር እየተገናኘን እርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።
ደግሞም እግዚአብሔርን ለማያመልኩ ሁሉ የመቀጣጫ ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ፈረደባቸው፤
እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው።
በዚህ ዓለም እኛ የምንኖረው ልክ ክርስቶስ እንደሚኖረው እንደ መሆኑ ፍቅራችን ፍጹም ቢሆን በፍርድ ቀን ያለ ፍርሀት በፊቱ ለመቅረብ ሙሉ መተማመን ይኖረናል።
እንዲሁም ማዕርጋቸውን ባለመጠበቅ ስፍራቸውን የተዉትን መላእክት አስታውሱ፤ እነርሱን እግዚአብሔር እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ በዘለዓለም እስራት፥ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ጠብቆ አቆይቷቸዋል።
በዚሁ ዐይነት ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችም ሴሰኞች ሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪም ዝሙት ፈጸሙ። ስለዚህ እነርሱ በዘለዓለም እሳት ለሚቀጡት ምሳሌ ሆነዋል።