እርሱ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለምትሰጡት አገልግሎት የድካም ዋጋችሁ ስለ ሆነ የተረፈውንም እናንተና ቤተሰቦቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ሆናችሁ መመገብ ትችላላችሁ፤
ማቴዎስ 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሠራተኛ ምግቡ የሚገባው ስለ ሆነ ለመንገዳችሁ ከረጢት፥ ትርፍ እጀ ጠባብ፥ ትርፍ ጫማ፥ በትርም አትያዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመንገዳችሁም ከረጢት፣ ትርፍ እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ የዕለት ጕርሱ ይገባዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመንገዳችሁ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። |
እርሱ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለምትሰጡት አገልግሎት የድካም ዋጋችሁ ስለ ሆነ የተረፈውንም እናንተና ቤተሰቦቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ሆናችሁ መመገብ ትችላላችሁ፤
እንዲህም አላቸው፦ “ለመንገዳችሁ የሚሆን ምንም አትያዙ፤ በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ ስንቅም ቢሆን፥ ገንዘብም ቢሆን፥ ቅያሬ ልብስም እንኳ ቢሆን አትያዙ።
በትሩን አንሥቶ፥ ከወንዝ ዳር አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች መርጦ በመልቀም በእረኝነት ኮረጆው ከተተ፤ ወንጭፉንም ይዞ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ።
ሳኦልም “መሄዱንስ እንሂድ፤ ነገር ግን ለዚያ ለእግዚአብሔር ሰው ምን ዐይነት ስጦታ ልናበረክትለት እንችላለን፤ ስንቃችንም እንኳ ከስልቻችን አልቆአል፤ ታዲያ ሌላ የምንሰጠው ነገር አለ እንዴ?” አለው።