ስለዚህ ማንነትዋን ለማወቅ ዳዊት አንድ መልእክተኛ ልኮ ቤርሳቤህ ተብላ የምትጠራው የኤሊዓም ልጅ፥ የሒታዊው የኦርዮ ሚስት መሆንዋን ተረዳ።
ማቴዎስ 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤ |
ስለዚህ ማንነትዋን ለማወቅ ዳዊት አንድ መልእክተኛ ልኮ ቤርሳቤህ ተብላ የምትጠራው የኤሊዓም ልጅ፥ የሒታዊው የኦርዮ ሚስት መሆንዋን ተረዳ።
እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤልም ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው።
እግዚአብሔር ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሒታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር በማድረጉና ትእዛዙንም በብርቱ ጥንቃቄ በመጠበቁ ነው።
በዚያም ብዙ ወንዶች ልጆችን ወለደ። የዓሚኤል ልጅ ቤርሳቤህ ሺምዓ፥ ሾባብ፥ ናታንና ሰሎሞን ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት።
ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።
እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ከንጉሥነት ስለ ሻርኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ድረስ ነው? እኔ እርሱ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ ይኖር ዘንድ አልፈልገውም። ይልቅስ የወይራ ዘይት በቀንድ ሞልተህ በመያዝ በቤተልሔም ወደሚኖረው እሴይ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ዘንድ ሂድ፤ እኔ ከእርሱ ልጆች መካከል አንዱን ንጉሥ እንዲሆን መርጬአለሁ።”
ዳዊት በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም የሚኖር የኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር፤ እሴይ ስምንት ልጆች ያሉት ሲሆን ሳኦል በነገሠበት ዘመን በዕድሜ የገፋ ሽማግሌ ሰው ነበር።
በእኔስ ላይ ሤራ የምታካሄዱት ስለዚህ ነውን? የገዛ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር መተባበሩን የነገረኝ ከእናንተ አንድ እንኳ የለም፤ ስለ እኔ የሚያስብ ከቶ ማንም የለም፤ ወይም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ አገልጋዬ በእኔ ላይ እንዲሸምቅ ልጄ ያነሣሣው መሆኑን ከእናንተ ማንም የነገረኝ የለም።”