ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሕዝቡን አሰናብቶ ወደ ቤት ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፥ “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ትርጒም አስረዳን” አሉት።
ማርቆስ 8:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተመገቡት ሰዎች አራት ሺህ ያኽል ነበሩ፤ ኢየሱስ እነርሱን አሰናበታቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም አራት ሺሕ ያህል ሰዎች ነበሩ፤ ካሰናበታቸውም በኋላ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም አራት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱንም አሰናበታቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ፤ አሰናበታቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሕዝቡን አሰናብቶ ወደ ቤት ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፥ “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ትርጒም አስረዳን” አሉት።
ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት የተጻፈው ሁሉ በዚያ ይፈጸማል።