ማርቆስ 8:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐይነ ስውሩም ቀና ብሎ፥ “አዎ ሰዎች ይታዩኛል፤ ግን እንደሚራመዱ ዛፎች ይመስላሉ፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ቀና ብሎ አይቶ፣ “ሰዎች እንደ ዛፍ ሲንቀሳቀሱ አያለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ቀና ብሎ አይቶ፥ “ሰዎች እንደ ዛፍ ሲንቀሳቀሱ አያለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሻቅቦም “ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ፤” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሻቅቦም፦ ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ አለ። |
እርሱም ማየት የተሳነውን ሰው እጅ ይዞ እየመራ ከመንደር ወደ ውጪ አወጣው፤ በሰውየውም ዐይኖች ላይ ምራቁን እንትፍ ብሎ እጁን ጫነበትና “አንዳች ነገር ታያለህን?” ሲል ጠየቀው።
ጋዓልም እነርሱን አይቶ ዘቡልን “ተመልከት! ሰዎች ከተራራው ጫፍ ላይ እየወረዱ ነው!” አለው። ዘቡልም “እነርሱ በተራሮች ላይ የሚታዩ ጥላዎች እንጂ ሰዎች አይደሉም” ሲል መለሰለት።