አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሥርዓተ ቀብር በሚፈጽምበት ሰዓት ከእነዚያ አደጋ ጣዮች መካከል አንድ ቡድን ሲመጣ ስለ ታየ፥ የሚቀበረውን ሬሳ ወደ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ በችኰላ በመወርወር ጥለውት ሸሹ፤ ያም ሬሳ ከኤልሳዕ አስከሬን ጋር በተገናኘበት ቅጽበት ወዲያውኑ ከሞት ተነሥቶ ቆመ።
ማርቆስ 5:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም የኢየሱስን ዝና ሰምታ ስለ ነበር በሚጋፋው ሕዝብ መካከል ከበስተኋላው መጥታ ልብሱን ነካች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ኢየሱስም በሰማች ጊዜ፣ ከበስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ነካች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ኢየሱስም በሰማች ጊዜ፥ ከበስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ነካች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢየሱስንም ወሬ ሰምታ በስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢየሱስንም ወሬ ሰምታ በስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች፦ |
አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሥርዓተ ቀብር በሚፈጽምበት ሰዓት ከእነዚያ አደጋ ጣዮች መካከል አንድ ቡድን ሲመጣ ስለ ታየ፥ የሚቀበረውን ሬሳ ወደ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ በችኰላ በመወርወር ጥለውት ሸሹ፤ ያም ሬሳ ከኤልሳዕ አስከሬን ጋር በተገናኘበት ቅጽበት ወዲያውኑ ከሞት ተነሥቶ ቆመ።
በየሄደበትም ስፍራ ሁሉ በመንደር፥ በከተማ፥ በገጠርም በሽተኞችን ወደ አደባባይ እያወጡ በእርሱ ፊት ያቀርቡአቸው ነበር፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳ እንዲነኩ ይለምኑት ነበር፤ የነኩትም ሁሉ ይድኑ ነበር።
በዚህም ምክንያት የጳውሎስን አካል የነካውን ልብስና መሐረብ እየወሰዱ በሽተኞቹን ሲያስነኩአቸው ከበሽታቸው ይፈወሱ ነበር፤ ርኩሳን መናፍስትም ይወጡላቸው ነበር።
ሰዎች ብዙ በሽተኞችን ወደ መንገድ እያወጡ በአልጋ ላይና በቃሬዛ ላይ ያስተኙአቸው ነበር፤ እንዲህም ያደረጉት ጴጥሮስ በዚያ በኩል ሲያልፍ ጥላው እንኳ በአንዳንዶቹ ላይ እንዲያርፍባቸው ነበር።