ማርቆስ 5:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ጀልባው በመግባት ላይ ሳለ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው፦ “እባክህ ልከተልህ!” ብሎ ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ወደ ጀልባዪቱ በሚገባበት ጊዜ፣ አጋንንት ዐድረውበት የነበረው ሰው ዐብሮት ለመሆን ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ወደ ጀልባዪቱ በሚገባበት ጊዜ፥ በአጋንንት ተይዞ የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር አብሮት ለመሆን ለመነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው። |
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
በታላቅ ድምፅም እየጮኸ፥ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? በእግዚአብሔር ስም እለምንሃለሁ፤ እባክህ አታሠቃየኝ!” አለው።