ማርቆስ 4:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመልካም መሬት የተዘራው ግን የሚያመለክተው ቃሉን ሰምተው በማስተዋል የሚቀበሉትን ሰዎች ነው። እንዲህ ዐይነቱ አንዱ ሠላሳ፥ አንዱ ሥልሳ፥ አንዱም መቶ ፍሬ ያፈራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎቹ በመልካም መሬት ላይ የተዘራውን ዘር ይመስላሉ፤ እነዚህም ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉና ሠላሳ፣ ስድሳ፣ መቶም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው። |
በመልካም መሬት ላይ የተዘራው የሚያመለክተው፥ ቃሉን ሰምቶ በማስተዋል የሚቀበለውን ሰው ነው፤ እርሱ ፍሬ ያፈራል፤ አንዱ መቶ፥ አንዱ ሥልሳ፥ አንዱ ሠላሳ ፍሬ ይሰጣል።”
በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ግን በመልካምና በቅን ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁትን ነው፤ እነርሱ በቃሉ ጸንተው ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል።
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእናንተም ሁኔታ እንደዚሁ ነው፤ እናንተ የክርስቶስ አካል ክፍል ስለ ሆናችሁ በሞት የመለየትን ያኽል ከሕግ ተለይታችኋል፤ ስለዚህ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ፍሬ እንድናፈራ ከሞት የተነሣው የክርስቶስ ወገኖች ሆናችኋል።
እንዲሁም ለጌታ ተገቢ በሆነ መንገድ በመኖር እርሱን በፍጹም እንድታስደስቱ ማናቸውንም መልካም ሥራ በመሥራት ፍሬ እንድታፈሩና እግዚአብሔርንም በማወቅ እያደጋችሁ እንድትሄዱ እንጸልያለን።
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ ከእኛ ተምራችኋል፤ አሁንም የምትኖሩት እንዲሁ ነው፤ በጌታ በኢየሱስ ስም የምንለምናችሁና የምንመክራችሁም ከዚህ በፊት ካደረጋችሁት ይበልጥ እንድታደርጉ ነው።