ማርቆስ 3:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ሁሉ የዘለዓለም ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ከቶ ኃጢአቱ ይቅር አይባልለትም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ሁሉ የዘላለም ኀጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘለዓለም ጥፋት ይሆንበታል እንጂ ለዘለዓለም አይሰረይለትም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኀጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም። |
“በሰው ልጅ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር በደሉ ይቅር ይባልለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር ግን በደሉ ይቅር አይባልለትም።
የአሳፋሪ ድርጊታቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ፥ እንደ ተቈጣ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም እንደሚጠብቃቸውና፥ እንደሚንከራተቱ ኮከቦች ናቸው።
በዚሁ ዐይነት ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችም ሴሰኞች ሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪም ዝሙት ፈጸሙ። ስለዚህ እነርሱ በዘለዓለም እሳት ለሚቀጡት ምሳሌ ሆነዋል።