ማርቆስ 3:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ፥ ለማስተማርም እንዲልካቸው ዐሥራ ሁለቱን መርጦ “ሐዋርያት” ብሎ ሰየማቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ጋራ እንዲሆኑ፣ ለስብከትም እንዲልካቸው ዐሥራ ሁለቱን ሾማቸው፤ ሐዋርያትም ብሎ ጠራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ጋር እንዲሆኑና ለመስበክም እንዲልካቸው ዐሥራ ሁለቱን መርጦ “ሐዋርያት” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥ |
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ፥ በሰማርያ፥ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
በሰዎች ወይም በሰው አማካይነት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስና እርሱንም ከሞት ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ ሆኜ ከተላክሁ ከእኔ ከጳውሎስ፥