ማርቆስ 14:70 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን እንደገና ካደ። ጥቂት ቈየት ብሎም በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፥ “የገሊላ ሰው መሆንህን በእርግጥ አነጋገርህ ያስረዳል፤ ስለዚህ በእርግጥ አንተም ከእነርሱ ወገን ነህ፤” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን አሁንም ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፣ “የገሊላ ሰው እንደ መሆንህ መጠን፣ በርግጥ አንተ ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን አሁንም ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፥ በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፥ “የገሊላ ሰው እንደ መሆንህ መጠን፥ በእርግጥ አንተ ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ደግሞ ካደ። ጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስን “የገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ፤” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ደግሞ ካደ። ጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስን፦ የገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ አሉት። |
“እስቲ ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ እርሱ ግን “ሺ” የሚለውን ፊደል አስተካክሎ መናገር ስለማይችል “ሲቦሌት” ይላል፤ ከዚህ በኋላ እርሱን ይዘው የዮርዳኖስ መሸጋገሪያ ከሆኑት ስፍራዎች በአንዱ ይገድሉታል፤ ያንጊዜም በዚሁ ዐይነት አርባ ሁለት ሺህ የኤፍሬም ሰዎች ተገደሉ።