ሉቃስ 9:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐዋርያት ከተላኩበት ተመልሰው መጡና ያደረጉትን ሁሉ ለኢየሱስ ነገሩት። እርሱም በቤተ ሳይዳ ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው ገለልተኛ ቦታ ብቻቸውን ይዞአቸው ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐዋርያትም ተመልሰው በመጡ ጊዜ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት፤ እርሱም ይዟቸው ቤተ ሳይዳ ወደምትባል ከተማ በመሄድ ለብቻው ገለል አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐዋርያትም ተመልሰው ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት። እነርሱን ይዞ፥ ለብቻው ወደ ገለልተኛ ሰፈር፥ ቤተሳይዳ ወደምትባል ከተማ፥ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት፤ እርሱም ለብቻቸው ይዞአቸው ቤተ ሳይዳ ከምትባል ከተማ አጠገብ ወደ አለ ምድረ በዳ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐዋርያትም ተመልሰው ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት። ከእርሱ ጋርም ወስዶአቸው ቤተ ሳይዳ ከምትባል ከተማ አጠገብ ወደ ምድረ በዳ ለብቻው ፈቀቅ አለ። |
“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት፥ በጢሮስና በሲዶና ከተሞች ተደርገው ቢሆን ኖሮ በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የሐዘን ልብስ ለብሰውና ዐመድ በላያቸው ላይ ነስንሰው ገና ዱሮ ንስሓ በገቡ ነበር!
ሰባ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከተላኩበት በጣም ደስ ብሎአቸው ተመለሱ፤ ወደ ኢየሱስም ቀርበው፦ “ጌታ ሆይ! በአንተ ስም አጋንንት እንኳ ታዘውልናል” አሉት።
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ በሥልጣናቸውም ሥር ሁኑ፤ እነርሱ የሚጠየቁበት ኀላፊነት ስላለባቸው ስለ ነፍሳችሁ ጉዳይ ይተጋሉ፤ እናንተ ብትታዘዙአቸው እነርሱ ሥራቸውን በደስታ ያከናውናሉ፤ ያለበለዚያ ሥራቸውን በሐዘን ይሠራሉ፤ ይህም እናንተን የሚጠቅም አይሆንም።