ሉቃስ 7:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስምዖንም፦ “ብዙ ዕዳ የቀረለት ሰው አብልጦ የሚወደው ይመስለኛል፤” ሲል መለሰ። ኢየሱስም “መልስህ ልክ ነው፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስምዖንም፣ “ብዙው ዕዳ የተተወለት ይመስለኛል” ሲል መለሰ። ኢየሱስም፣ “ትክክል ፈርደሃል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምዖንም ሲመልስ፦ “ብዙ የተወለትን ይመስለኛል፤” አለ። እርሱም፦ “በትክክል ፈረድህ፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምዖንም መልሶ፥ “ብዙውን የተወለት ነው እላለሁ” አለው፤ እርሱም፥ “መልካም ፈረድህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስምዖንም መልሶ፦ ብዙ የተወለቱ ይመስለኛል አለ። እርሱም፦ በእውነት ፈረድህ አለው። |
ኢየሱስም የሕግ መምህሩ በጥበብና በማስተዋል እንደ መለሰ አይቶ፥ “አንተስ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም፤” አለው። ከዚህ በኋላ ለኢየሱስ ጥያቄ ሊያቀርብለት የደፈረ ማንም የለም።
ሁለቱም የተበደሩትን መክፈል ቢያቅታቸው አበዳሪው ዕዳቸውን ተወላቸው፤ ታዲያ፥ ከሁለቱ ባለዕዳዎች፥ አበዳሪውን አብልጦ የሚወድ የትኛው ይመስልሃል?” አለው።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሴትዮዋ መለስ ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ስገባ አንተ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብክልኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን በእንባዋ አጥባ በጠጒርዋ አበሰችው።