ሉቃስ 7:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ የማይሰናከል የተባረከ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ የማይሰናከል ሁሉ ብፁዕ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔም የማይሰናከል ብፁዕ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔም የማይሰናከል ብፁዕ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው አላቸው። |
ስምዖን ከባረካቸው በኋላ በተለይ የሕፃኑን እናት ማርያምን እንዲህ አላት፦ “እነሆ! ይህ ሕፃን በእስራኤል ውስጥ ለብዙዎቹ የመጥፋት፥ ለብዙዎቹ ግን የመዳን ምክንያት ይሆናል፤ እርሱም ብዙዎች የማይቀበሉት ምልክት ይሆናል።
ኢየሱስ መልእክተኞቹን እንዲህ አላቸው፦ “ተመልሳችሁ ሂዱና ለዮሐንስ ያያችሁትንና የሰማችሁትን ንገሩት፤ እነሆ፥ ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ቀጥ ብለው ይሄዳሉ፤ ለምጻሞች ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድኾችም ወንጌል ይሰበካል።
የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ እያለ ይናገር ጀመር፦ “ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን?
የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሥጋዊ ሰው ግን ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጠውን ስጦታ መቀበል አይችልም፤ የስጦታው ታላቅነት የሚመረመረው በእግዚአብሔር መንፈስ አማካይነት ስለ ሆነ ሊያስተውለው አይችልም፤ እንዲያውም ይህ ለእርሱ ሞኝነት መስሎ ይታየዋል።