በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አንቺ ሴት እምነትሽ! ትልቅ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ!” አላት። የሴትዮዋም ልጅ በዚያኑ ሰዓት ዳነች።
ሉቃስ 7:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተላኩትም ሰዎች ወደ መቶ አለቃው ቤት ተመልሰው በመጡ ጊዜ አገልጋዩን ድኖ አገኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተላኩት ሰዎችም ወደ ቤት በተመለሱ ጊዜ፣ ባሪያውን ድኖ አገኙት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተላኩትም ወደ ቤት ተመልሰው ኣገልጋዩን በመልካም ጤንነት ላይ ሆኖ አገኙት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተላኩትም በተመለሱ ጊዜ ብላቴናውን ድኖ አገኙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተላኩትም ወደ ቤት ተመልሰው ባሪያውን ባለ ጤና ሆኖ አገኙት። |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አንቺ ሴት እምነትሽ! ትልቅ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ!” አላት። የሴትዮዋም ልጅ በዚያኑ ሰዓት ዳነች።
ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ ተደነቀ፤ ወደሚከተሉትም ሰዎች መለስ ብሎ፥ “በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ እምነት ከቶ አላገኘሁም እላችኋለሁ፤” አላቸው።