ሉቃስ 24:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ይህን የሆነውን ነገር ሁሉ አንሥተው እርስ በእርሳቸው ይወያዩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርስ ይነጋገሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸውም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ ይነጋገሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። |
በዚያኑ ቀን ከኢየሱስ ተከታዮች ሁለቱ ከኢየሩሳሌም ዐሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ያኽል ርቃ ወደምትገኝ ኤማሁስ ተብላ ወደምትጠራ መንደር ይጓዙ ነበር።
ስለዚህ ደግ ሰው ከመልካም ልቡ መልካምን ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከመጥፎ ልቡ ክፉውን ነገር ያወጣል። ሰው በአፉ የሚናገረው ከልቡ ሞልቶ የተረፈውን ነው።
እነዚህኑ ትእዛዞች ለልጆችህ አስተምራቸው፤ በቤት ስትቀመጥም ሆነ በመንገድ ስትሄድ፥ ዕረፍት በምታደርግበትም ጊዜ ሆነ ሥራ በምትሠራበት ጊዜ ሁሉ፥ እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር አሰላስል፤