ሉቃስ 22:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም በነገሩ ተደስተው ገንዘብ ሊሰጡት ተዋዋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በዚህ ደስ አላቸው፣ ገንዘብ ሊሰጡትም ተዋዋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ደስ አላቸው፤ ገንዘብም ሊሰጡት ተዋዋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስ ብሏቸውም ሠላሳ ብር ሊሰጡት ተስማሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ደስ አላቸው፥ ገንዘብም ሊሰጡት ተዋዋሉ። |
እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ጠፍተዋል፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ተሳስተዋል።
እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!