ሉቃስ 22:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “አሁን ግን የገንዘብ ቦርሳም ሆነ ከረጢት ያለው ይያዝ፤ ሰይፍም የሌለው ልብሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “አሁን ግን ኰረጆም፣ ከረጢትም ያለው ሰው ይያዝ፤ ሰይፍ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ይግዛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “አሁን ግን ቦርሳ ያለው ይያዘው፤ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮጆውን ይያዝ፤ ከረጢትም ያለው እንዲሁ ያድርግ፤ ሰይፍ የሌለውም ልብሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አሁን ግን ኮረጆ ያለው ከእርሱ ጋር ይውሰድ፥ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “የገንዘብ ቦርሳ፥ ከረጢት፥ ጫማም ሳትይዙ በላክኋችሁ ጊዜ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱም “ምንም የጐደለብን ነገር አልነበረም” ሲሉ መለሱለት።
ስለ እኔ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም ስለሚገባው ‘ከዐመፀኞች ጋር ተቈጠረ’ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል በእኔ ላይ መፈጸም አለበት እላችኋለሁ።”
ይህን ለእናንተ መናገሬ በእኔ ሆናችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ብዬ ነው፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፥ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
ክርስቶስ በሥጋው መከራ የተቀበለ ስለ ሆነ እናንተም የጦር መሣሪያን እንደ ታጠቀ ሰው በዚህ ሐሳብ በርትታችሁ ተዘጋጁ፤ በሥጋው መከራን የተቀበለ ሰው ኃጢአት መሥራትን አቋርጧል።