አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።
ሉቃስ 20:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ “ከየት እንደ ሆነ አናውቅም” ሲሉ መለሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ “ከየት እንደ ሆነ አናውቅም” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልሰውም “ከየት እንደሆነ አናውቅም፤” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወዴት እንደ ሆነች አናውቅም” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልሰውም፦ ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም አሉት። |
አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።
አስደናቂ ተአምርን አከታትዬ በማምጣት ይህ ሕዝብ እንዲገረም አደርገዋለሁ፤ የጥበበኞች ጥበብ ትሰወራለች፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትረሳለች።”
ዞር ብዬ በተመለከትኩ ጊዜ ማንም አልነበረም፤ ከአማልክትም መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም፤ ጥያቄም ስጠይቅ ማንም መልስ የሚሰጥ አልነበረም።
መንጋውን ለከዳ ለእንዲህ ዐይነቱ ዋጋቢስ እረኛ ወዮለት! ክንዱና ቀኝ ዐይኑ በሰይፍ ይመታ፤ ክንዱ በፍጹም ይድረቅ፤ ቀኝ ዐይኑም ጨርሶ ይጥፋ።”