ሉቃስ 20:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሙታን አይነሡም” የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንሣኤ የለም ከሚሉት ሰዱቃውያን አንዳንዶቹ ወደ ኢየሱስ መጥተው ጥያቄ አቀረቡለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሙታንን ትንሣኤ የሚክዱ ሰዱቃውያን ቀርበው ጠየቁት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሙታን አይነሡም” ከሚሉ ከሰዱቃውያንም አንዳንድ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትንሣኤ ሙታንንም የሚክዱ ከሰዱቃውያን አንዳንዶቹ ቀርበው ጠየቁት፥ |