የእስራኤል ሕዝብ ብዙ ዘለላ እንደ ያዘ የወይን ተክል ናቸው፤ ፍሬ በበዛላቸው መጠን ብዙ የጣዖት መሠዊያዎችን ሠሩ፤ ምድራቸው ፍሬያማ ሆና በበለጸገችላቸው መጠን የጣዖት መስገጃ ዐምዶችን አስጊጠው ሠሩ።
ሉቃስ 20:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሌላ አገልጋይ ቢልክ እርሱንም ደበደቡት፤ አዋርደውም ባዶ እጁን ሰደዱት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም ሌላ ባሪያውን ላከ፤ ገበሬዎቹም እርሱንም ደግሞ ደበደቡት፤ አዋርደውም ባዶ እጁን ሰደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ሌላ አገልጋይ ላከ፤ እነርሱም ያን ደግሞ ደበደቡት፥ አዋርደውም ባዶውን ሰደዱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም ሌላውን አገልጋዩን ላከ፤ እርሱንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን ሰደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጨምሮም ሌላውን ባሪያ ላከ፤ እነርሱም ያን ደግሞ ደበደቡት አዋርደውም ባዶውን ሰደዱት። |
የእስራኤል ሕዝብ ብዙ ዘለላ እንደ ያዘ የወይን ተክል ናቸው፤ ፍሬ በበዛላቸው መጠን ብዙ የጣዖት መሠዊያዎችን ሠሩ፤ ምድራቸው ፍሬያማ ሆና በበለጸገችላቸው መጠን የጣዖት መስገጃ ዐምዶችን አስጊጠው ሠሩ።
ወይኑ ባፈራ ጊዜ የወይኑ ተክል ባለቤት ከፍሬው ድርሻውን እንዲቀበልለት አንድ አገልጋይ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን አገልጋዩን ደብድበው፥ ባዶ እጁን ሰደዱት።
ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? እነርሱ የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ እናንተም አሁን ይህን ጻድቁን አሳልፋችሁ በመስጠት ገደላችሁት።
እናንተ እንደምታውቁት ከዚህ ቀደም በፊልጵስዩስ በነበርንበት ጊዜ መከራና ስድብ ደርሶብናል፤ ነገር ግን ታላቅ ተቃውሞ ቢደርስብንም እንኳ ወንጌሉን ለእናንተ እንድናስተምር አምላካችን ድፍረትን ሰጥቶናል።