ሉቃስ 17:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ አንዱ በእርሻ ሥራ የተሰማራ፥ ወይም በጎች የሚጠብቅ አገልጋይ ቢኖረው፥ አገልጋዩ ከሥራው በተመለሰ ጊዜ ወዲያውኑ ‘ና ተቀመጥና ራትህን ብላ’ ይለዋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ መካከል አንድ ሰው ዐራሽ ወይም በግ ጠባቂ የሆነ ባሪያ ቢኖረው፣ ከዕርሻ የተመለሰውን ባሪያውን፣ ‘ቶሎ ወደ ማእድ ቅረብ’ ይለዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ አገልጋይ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ ‘ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ፤’ የሚለው ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አራሽ ወይም ከብት ጠባቂ አገልጋይ ያለው ከእናንተ ማን ነው? ከእርሻው በተመለሰ ጊዜ ጌታው ና፥ ፈጥነህ ወደዚህ ውጣና ከእኔ ጋር በማዕድ ተቀመጥ ይለዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ፦ ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለው ማን ነው? |
ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተስ እያንዳንዱ በሰንበት ቀን በሬውን ከተዘጋበት አውጥቶ፥ ወይም አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ውሃ ወደሚያጠጣበት ቦታ ይወስደው የለምን?
ጌታ ኢየሱስም “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ በባሕር ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዝላችኋል” አላቸው።
ይልቅስ፥ ‘በል! ራቴን አዘጋጅልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣም አደግድገህ አገልግለኝ፤ ከዚህ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ፥ ትጠጣለህ’ ይለው የለምን?