ሉቃስ 17:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ያድናታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሱን ለማሰንበት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ነፍሱን የሚያጠፋት ግን ያቈያታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕይወቱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን የሚያጠፋ ሁሉ ይጠብቃታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሱን ሊያድናት የሚወድ ይጣላት፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚጥላትም ያድናታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም የሚያጠፋ ሁሉ በሕይወት ይጠብቃታል። |
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።