ሉቃስ 16:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምም ‘የሙሴና የነቢያት መጻሕፍት የሚሉትን ካልሰሙማ አንድ ሰው ከሞት ተነሥቶ ቢነግራቸውም አያምኑትም’ አለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አብርሃምም፣ ‘ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ፣ አንድ ሰው ከሙታን ቢነሣ እንኳ አያምኑም’ አለው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ሰው ቢነሣ አያምኑም፤’ አለው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም፦ ‘ሙሴንና ነቢያትን ካልሰሙማ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ቢኖርም እንኳ አይሰሙትም፤ አያምኑትምም’ አለው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው። |
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “ሰዎችን አሰናክለው ወደ ኃጢአት የሚጥሉ ነገሮች መምጣታቸው አይቀርም፤ ነገር ግን የኃጢአትን መሰናክል ለሚያመጣው ለዚያ ሰው ወዮለት!
ቀን ከቀጠሩለትም በኋላ ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ፤ እርሱም ከጧት እስከ ማታ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በመመስከር አሳቡን ገለጠላቸው፤ እነርሱንም ለማሳመን ከሙሴ ሕግና ከነቢያት መጻሕፍት እየጠቀሰም ስለ ኢየሱስ አስረዳቸው።
ጌታን መፍራት ምን መሆኑን ስለምናውቅ ሰዎችን እናስረዳለን፤ እኛ ምን መሆናችንንም እግዚአብሔር ያውቃል፤ እናንተም በልቡናችሁ ምን መሆናችንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።