እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
ሉቃስ 15:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ ያንተ ልጅ ልባል አይገባኝም፤ ነገር ግን ከቅጥረኞች አገልጋዮችህ እንደ አንዱ አድርገኝ ልበለው።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም፤ ከተቀጠሩት አገልጋዮችህ እንደ አንዱ ቍጠረኝ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከተቀጣሪዎችህ እንደ አንዱ አድርገኝ፤”’ እለዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ወዲህስ ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ አድርገኝ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ። |
እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
በሌላ ስፍራ አንድ ሺህ ቀን ከመቈየት በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው፤ በክፉዎች ቤት ከምኖር ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት ዘበኛ ሆኜ መኖርን እመርጣለሁ።