La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 15:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታናሽዮው አባቱን ‘አባባ፥ ከሀብትህ ከፍለህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው። ስለዚህ አባትየው ሀብቱን ለሁለት ልጆቹ አካፈለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእነርሱም ታናሹ ልጅ አባቱን፣ ‘አባቴ ሆይ፤ ከሀብትህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው፤ አባትየውም ሀብቱን ለልጆቹ አካፈላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእነርሱም ታናሹ አባቱን ‘አባቴ ሆይ! ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ፤’ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ታናሹ ልጁም አባ​ቱን፦ ‘አባቴ ሆይ፥ ከገ​ን​ዘ​ብህ የሚ​ደ​ር​ሰ​ኝን ከፍ​ለህ ስጠኝ’ አለው፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ከፍሎ ሰጠው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእነርሱም ታናሹ አባቱን፦ አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።

Ver Capítulo



ሉቃስ 15:12
7 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።


ሌሎቹ ሁሉ የሰጡት ካላቸው ሀብት የተረፋቸውን ነው፤ እርስዋ ግን ድኻ ሆና ሳለች ምንም ሳታስቀር ያላትን ሁሉ ሰጠች።”


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤


ከጥቂት ቀን በኋላ ታናሽዮው ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ በዚያም አገር ገንዘቡን ሁሉ በከንቱ አባከነ።


ይህ ልጅህ ግን ሀብትህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በተመለሰ ጊዜ የሰባውን ወይፈን ዐረድክለት።’