ሉቃስ 15:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀራጮችና ኃጢአተኞች ሁሉ ትምህርቱን ለመስማት ተሰብስበው ወደ ኢየሱስ መጥተው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ቀን፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኀጢአተኞች ሁሉ ሊሰሙት በዙሪያው ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀራጮችና ኀጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀራጮችና ኀጢኣተኞችም ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። |
“ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ሁሉ የባስሁ ኃጢአተኛ እኔ ነኝ።