ሉቃስ 14:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ለግብዣ የተጠሩ ሰዎች የክብር ስፍራ ለመያዝ ሲሽቀዳደሙ አየ፤ ስለዚህ ይህን ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ተጋባዦቹ የክብር ስፍራ ሲመርጡ ተመልክቶ፣ እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ለእነርሱ ነገራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታደሙትንም የከበሬታ ስፍራ እንደ መረጡ ተመልክቶ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምሳ ላይ ለነበሩትም ወደ ላይኛው ወንበር ሲሽቀዳደሙ ባያቸው ጊዜ ምሳሌ መስሎ አስተማራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የታደሙትንም የከበሬታ ስፍራ እንደ መረጡ ተመልክቶ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ |
“እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኲራብ ውስጥ በክብር ወንበር ላይ መቀመጥ ትወዳላችሁ፤ እንዲሁም በአደባባይና በገበያ ቦታ ሰው ሁሉ እጅ እንዲነሣችሁ ትፈልጋላችሁ።
“ረጃጅም ልብስ ለብሰው ወዲያና ወዲህ መዞርን፥ በገበያም የክብር ሰላምታ መቀበልን፥ በምኲራብ የክብር ወንበርን፥ በግብዣም የክብር ስፍራን ከሚወዱ ከሕግ መምህራን ተጠንቀቁ።
በትሕትና ተሞልታችሁ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ አድርጋችሁ ቊጠሩ እንጂ በራስ ወዳድነት ወይም “ያለ እኔ ማን አለ” በሚል ትምክሕት ምንም ነገር አታድርጉ።
ሶምሶንም እንዲህ አላቸው፤ “እስቲ ታውቁ እንደ ሆነ አንድ እንቆቅልሽ ልንገራችሁ፤ በሰባቱ የሠርጉ በዓል ቀኖች ውስጥ ይህን እንቆቅልሽ ፈትታችሁ ብትነግሩኝ፥ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ቅያሬ ልብስ እሰጣችኋለሁ፤