ሉቃስ 14:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዩም ተመልሶ መጣና ጌታውን ‘ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ ያዘዝከኝን ሁሉ ፈጽሜአለሁ፤ ሆኖም ገና ትርፍ ቦታ አለ’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ባሪያውም፣ ‘ጌታዬ፤ ያዘዝኸው ሁሉ ተፈጽሟል፤ ገና አሁንም ቦታ አለ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዩም ‘ጌታ ሆይ! እንዳዘዝኸኝ ተደርጎአል፤ ሆኖም ገና ስፍራ አለ፤’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ አገልጋዩ፦ አቤቱ እንደ አዘዝኸኝ አደረግሁ፤ ገናም ቦታ አለ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያውም፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳዘዝኸኝ ተደርጎአል፥ ገናም ስፍራ አለ አለው። |
“አገልጋዩም ወደ ቤት ተመልሶ ይህን ሁሉ ለጌታው ነገረው፤ የቤቱም ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን ‘ቶሎ ብለህ ወደ ከተማው ጐዳናዎችና ስላች መንገዶች ሂድ፤ ድኾችን፥ አካለ ስንኩሎችን፥ ዕውሮችን፥ አንካሶችንም ጠርተህ አምጣልኝ’ አለው።
ስለዚህ የቤቱ ጌታ አገልጋዩን እንዲህ አለው፦ ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ገጠር በሚወስዱት ጐዳናዎችና ስላች መንገዶች ሂደህ ሌሎች እንዲመጡ አድርግ!
እኔ ከቅዱሳን ሁሉ የማንስ ብሆንም እንኳ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ እንዳበሥር በእግዚአብሔር ጸጋ ይህ ዕድል ተሰጠኝ።