የሚሰማብኝ የለም ብለህ በስውር እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትማ፤ በተኛህበት አልጋህ ላይ ሆነህም ባለጸጋን አትስደብ፤ ምሥጢርህን የሰሙ ነገር ጠላፊዎች ክንፍ እንዳለው ወፍ በረው ሊነግሩብህ ይችላሉ።
ሉቃስ 12:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በጨለማ የተናገራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በዝግ ቤት ውስጥ በሹክሹክታ በጆሮ የተናገራችሁትም በሰገነት ላይ በይፋ ይነገራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በጨለማ ያወራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ ያንሾካሾካችሁት በሰገነት በይፋ ይነገራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በጨለማ የተናገራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይታወጃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጨለማ የምትናገሩት በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትንሾካሾኩት በሰገነት ይሰበካል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። |
የሚሰማብኝ የለም ብለህ በስውር እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትማ፤ በተኛህበት አልጋህ ላይ ሆነህም ባለጸጋን አትስደብ፤ ምሥጢርህን የሰሙ ነገር ጠላፊዎች ክንፍ እንዳለው ወፍ በረው ሊነግሩብህ ይችላሉ።