ሉቃስ 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ ያ ወዳጁ ከውስጥ ሆኖ፥ ‘እባክህ አታስቸግረኝ! በሩ ተቈልፎአል፤ ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል፤ ስለዚህ ተነሥቼ የፈለግኸውን እንጀራ ልሰጥህ አልችልም፤’ ይለዋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቤት ውስጥ ያለውም፣ ‘አታስቸግረኝ፤ በሩ ተቈልፏል፤ ልጆቼም ዐብረውኝ ተኝተዋል፤ ከእንግዲህ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም’ ይለዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያም ከውስጥ መልሶ፦ ‘አታስቸግረኝ፤ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ናቸው፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም፤’? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያ ወዳጁም ከውስጥ ሆኖ፦ ‘አትዘብዝበኝ፤ ደጁን አጥብቀን ዘግተናል፤ ልጆችም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል፤ እሰጥህ ዘንድ መነሣት አልችልም’ ይለዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ከውስጥ መልሶ፦ አታድክመኝ፤ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ አሉ፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም ይላልን? |
ሞኞቹ ልጃገረዶች፥ ዘይት ለመግዛት በሄዱበት ወቅት ሙሽራው መጣ። ተዘጋጅተው የነበሩትም ልጃገረዶች ከሙሽራው ጋር ወደ ሠርጉ ግብዣ አዳራሽ ገቡ፤ በሩም ተዘጋ።
የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።
ስለዚህ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ የመቶ አለቃው ወዳጆቹን እንዲህ ሲል ወደ ኢየሱስ ላከ፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ወደ ቤቴ ትገባ ዘንድ ያልተገባሁ ነኝና ወደ ቤቴ ለመምጣት አትድከም።