ሉቃስ 11:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋል፤ ነገር ግን እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የነነዌ ሰዎችም በፍርድ ጊዜ ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ እነርሱ የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፣ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይነሳሉ፥ በእርሱም ላይ ይፈርዳሉ፤ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚች ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፋረዱአታል፤ ያሳፍሩአታልም፤ ዮናስ በሰበከላቸው ጊዜ ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነነዌ ሰዎች በፍርድ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ። |
እግዚአብሔርም “ስለዚህች ቅል ልትበሳጭ ይገባሃልን?” አለው። ዮናስም “በእርግጥ መበሳጨት ይገባኛል፤ እንዲያውም በንዴት እስከምሞት ድረስ መበሳጨት አለብኝ!” አለ።
እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ክፉና የማያምን ትውልድ ተአምር ለማየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ተአምር በቀር ሌላ ተአምር አይሰጠውም።
የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋልና። አሁን ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።
የደቡብ ንግሥት በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ በእርሱ ላይ ትፈርዳለች፤ እርስዋ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከዓለም ዳርቻ መጥታለች፤ ነገር ግን እነሆ፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ፤