ሉቃስ 11:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተመልሶ ሲመጣ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲመጣም ተጠርጎና ተስተካክሎ ያገኘዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጣም ጊዜ ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲመጣም ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል። |
“ርኩስ መንፈስ ከሰው ውስጥ በወጣ ጊዜ የሚያርፍበት ቦታ በመፈለግ ውሃ በሌለበት በደረቅ ምድር ሁሉ ይዞራል፤ የሚያርፍበት ቦታ ካላገኘ ግን ‘ወደወጣሁበት ቤቴ ተመልሼ ልሂድ’ ይላል።
ከዚህ በኋላ ሄዶ ከእርሱ ይብስ የከፉ ሌሎች ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል፤ ቀድሞ እርሱ በነበረበት ቤትም ገብተው በዚያ ይኖራሉ፤ የዚያም ሰው የመጨረሻ ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የባሰ ይሆናል።”