ሉቃስ 11:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እኔ አጋንንትን በብዔልዜቡል የማስወጣ ከሆንኩ ልጆቻችሁስ በማን ያስወጡአቸዋል? ስለዚህ የገዛ ልጆቻችሁ እንኳ ይፈርዱባችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ በማን ያወጧቸው ይሆን? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔስ በብዔልዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንኩ፥ ልጆቻችሁ በማን ያስወጣሉ? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆነ፥ ልጆቻችሁ በምን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ይፋረዱአችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። |
ስለዚህ ተማሪ እንደአስተማሪው፥ አገልጋይም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። የቤቱን ጌታ ‘ብዔልዜቡል’ ብለው ከጠሩት ቤተሰቦቹንማ ከዚህ በከፋ ስም እንዴት አይጠሩአቸውም!
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ጌታውም ‘አንተ መጥፎ አገልጋይ! በአነጋገርህ እፈርድብሃለሁ፤ እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የምሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆኔን ዐውቀሃል፤
ከዚህም በኋላ ዮሐንስ ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፤ ነገር ግን ከእኛ ጋር ስላልሆነ ከለከልነው፤” አለ።
አጋንንትን ከሰዎች እያስወጡ በየቦታው የሚዞሩ አንዳንድ አይሁድ “ጳውሎስ በሚሰብከው በጌታ ኢየሱስ ስም እንድትወጡ እናዛችኋለን” በማለት አጋንንትን ከሰዎች ለማስወጣት ይሞክሩ ነበር።
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።