La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 10:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእውነቱ ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት እናንተ የምታዩትን ለማየት ተመኝተው ነበር፤ ነገር ግን አላዩም፤ እናንተ የምትሰሙትንም ለመስማት ተመኝተው ነበር፤ ነገር ግን አልሰሙም።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እላችኋለሁና፤ ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ የምታዩትን ለማየት ፈልገው አላዩም፤ የምትሰሙትንም ለመስማት ፈልገው አልሰሙም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እላችኋለሁና፥ እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት ሊያዩ ወደዱ አላዩምም፤ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወደዱ አልሰሙምም።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብዙ ነቢ​ያ​ትና ነገ​ሥ​ታት እና​ንተ የም​ታ​ዩ​ትን ሊያዩ ተመኙ፤ አላ​ዩ​ምም፤ እና​ንተ የም​ት​ሰ​ሙ​ት​ንም ሊሰሙ ተመኙ፥ አል​ሰ​ሙም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እላችኋለሁና፥ እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት ሊያዩ ወደዱ አላዩምም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም አለ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 10:24
7 Referencias Cruzadas  

“የእናንተ ግን ዐይኖቻችሁ ስለሚያዩ፥ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ የተባረኩ ናቸው።


ቀጥሎም ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መለስ ብሎ ለብቻቸው እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የምታዩትን የሚያዩ የተባረኩ ናቸው።


አንድ ቀን አንድ የሕግ መምህር ወደ ኢየሱስ መጣ፤ ሊፈትነውም ፈልጎ “መምህር ሆይ! የዘለዓለምን ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባኛል?” ሲል ጠየቀው።


የአባታችሁ የአብርሃም ምኞት የእኔን ቀን አይቶ ለመደሰት ነበር፤ አይቶም ተደሰተ።”


እነዚህ ሁሉ በእምነት እንዳሉ ሞቱ፤ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውንም ነገር አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው ልክ እንዳገኙት አድርገው በደስታ ተቀበሉት። በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውንም ተገነዘቡ።


እነዚህ ሁሉ ስለ እምነታቸው የተመሰከረላቸው ቢሆኑም የተሰጣቸውን ተስፋ ገና አላገኙም።