የሻፋንን ልጅ አዛንያን ጨምሮ ሰባ የእስራኤላውያን መሪዎች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጥና ይዞ ነበር፤ ከጥናውም መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጢስ ይወጣ ነበር፤
ሉቃስ 10:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጌታ፥ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ እርሱ ሊሄድበት ወደአሰበውም ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ጌታ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መርጦ ሾመ፤ ወደሚሄድበትም ከተማና ቦታ ሁሉ እንዲቀድሙት፣ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ ሁለት ሁለትም አድርጎ ራሱ ሊሄድበት ወደአሰበው ከተማና ስፍራ ሁሉ አስቀድሞ ላካቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ጌታችን ሌሎች ሰባ ሰዎችን መረጠ፤ ሁለት ሁለት አድርጎም ሊሄድበት ወደ አለው ከተማና መንደር በፊቱ ላካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎቹን ሰብዓ ሾመ፥ ሁለት ሁለትም አድርጎ እርሱ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና ስፍራ ሁሉ በፊቱ ላካቸው። |
የሻፋንን ልጅ አዛንያን ጨምሮ ሰባ የእስራኤላውያን መሪዎች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጥና ይዞ ነበር፤ ከጥናውም መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጢስ ይወጣ ነበር፤
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሕዝብ አመራር በመስጠት የታወቁ ሰባ ሽማግሌዎችን ምረጥ፤ እነርሱንም ሰብስበህ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸውና በአጠገብህ ይቁሙ፤
ልክ እንደ ነቢዩ ኤልያስ በመንፈስና በኀይል ሆኖ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆቻቸው፥ የማይታዘዙትንም ሰዎች ልብ ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልሳል፤ ሕዝቡንም በማንቃት ለጌታ እንዲዘጋጅ ያደርጋል።”