ዘሌዋውያን 25:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእንስሶችህና በምድርህ ለሚገኙ አራዊት የሚበቃ ምግብ ታገኛለህ፤ ምድሪቱ የምታስገኘው ነገር ሁሉ ሊበላ ይችላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ለቤት እንስሳትህና በምድርህ ለሚኖሩ የዱር አራዊት ምድሪቱ የምታበቅለው ሁሉ መኖ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ለእንስሶችህ፥ በምድርህም ላሉት አራዊት እርሷ የምትሰጠው ሁሉ ለመኖ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእንስሶችህም፥ በምድርህም ላሉት አራዊት ፍሬዋ ሁሉ ምግብ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእንስሶችህም፥ በምድርህም ላሉት አራዊት ፍሬዋ ሁሉ መኖ ይሁን። |
በምድር ሰንበት ዓመት የሚበቅለው ሰብል ሁሉ ለአንተ፥ ለወንድ አገልጋይህ፥ ለሴት አገልጋይህ፥ ለቅጥረኛህ፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ጊዜያዊ መጻተኛ ምግብ ይሆናል።