La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 25:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን በሌዋውያን ከተሞች ዙሪያ የሚገኝ የግጦሽ ሣር መሬት ፈጽሞ አይሸጥም፤ እርሱ ለዘለዓለም ቀዋሚ ንብረታቸው ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በከተሞቻቸው ዙሪያ ያለው የግጦሽ መሬት ግን አይሸጥ፤ ለዘላለም ቋሚ ንብረታቸው ነውና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በከተማቸውም ዙሪያ ያለው መሰማሪያ የዘለዓለም ርስታቸው ነውና አይሸጥም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በከ​ተ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ዙሪያ ያሉ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የዘ​ለ​ዓ​ለም ርስ​ቶ​ቻ​ቸው ናቸ​ውና አይ​ሸ​ጡም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በከተማቸውም ዙሪያ ያለችው መሰምርያ የዘላለም ርስታቸው ናትና አትሸጥም።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 25:34
7 Referencias Cruzadas  

ለአሮን ልጆች በተመደቡ ከተሞች ወይም የእነዚህ ከተሞች ይዞታ በሆኑት የግጦሽ ቦታዎች ከሚኖሩት ካህናት መካከል ለካህናት ቤተሰቦችና በሌዋውያን ጐሣ የስም ዝርዝር በያዘ መዝገብ ውስጥ ስማቸው ለሚገኝ ወንዶች ሁሉ ምግብን ለማከፋፈል ኀላፊዎች የሆኑ ሰዎች ነበሩ።


ከካህናቱ ቦታ ጐን ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ዐሥር ሺህ ክንድ ወርድ የሆነ የሌዋውያን ድርሻ አለ፤ ጠቅላላውም ከካህናቱ ድርሻ ጋር ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ኻያ ሺህ ክንድ ወርድ ነው።


ለእግዚአብሔር የሚከለለው ስፍራ በምድሪቱ ከሚገኘው ሁሉ የተሻለ ምርጥ ቦታ ነው፤ ከእርሱም ተከፍሎ የሚሸጥና የሚለወጥ ወይም ለማንም በውርስ የሚተላለፍ አይሆንም፤ እርሱ ለእግዚአብሔር ተለይቶ የተቀደሰ ስፍራ ነው።


“ምድሪቱ ለዘለቄታ መሸጥ አይገባትም፤ እርስዋ የእኔ እንጂ የእናንተ አይደለችም፤ እናንተ እንደ መጻተኛ ሆናችሁ እንድትጠቀሙባት ብቻ ፈቅጃለሁ።


ሌዋውያን በገዛ ከተሞቻቸው የሚሠሩአቸው ቤቶች በእስራኤላውያን መካከል የእነርሱ ቀዋሚ ንብረቶች ናቸው። በእነዚህ ከተሞች ውስጥ አንድ ሌዋዊ ቤት ቢሸጥና መልሶ ለመዋጀት ባይችል በኢዮቤልዩ ዓመት ይመለስለታል፤