የወይን መከርህንም ስትሰበስብ በሐረጉ ላይ ተሰውሮ የቀረውን ወይም በመሬት ላይ የረገፈውን የወይን ዘለላ አጥርተህ ለመልቀም እንደገና ወደ ኋላ አትመለስ፤ ይህን ሁሉ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ዘሌዋውያን 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ድንበር ያለውን እህል አትጨዱ፤ ስታጭዱ የቀረውንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ፣ በዕርሻችሁ ዳርና ዳር ያለውን አትጨዱ፤ ቃርሚያውንም አትልቀሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን አጨዳ አታጥሩ፤ ስታጭዱም የወደቀውን ቃርሚያ አትልቀሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር ፈጽማችሁ አትጨዱ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ። |
የወይን መከርህንም ስትሰበስብ በሐረጉ ላይ ተሰውሮ የቀረውን ወይም በመሬት ላይ የረገፈውን የወይን ዘለላ አጥርተህ ለመልቀም እንደገና ወደ ኋላ አትመለስ፤ ይህን ሁሉ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ እግዚአብሔር ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከር በምታጭዱበት ጊዜ የመጀመሪያውን ነዶ ለካህኑ ስጡ፤
“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር አትጨዱ፤ የመከሩንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤ እርሱን ለድኾችና ለመጻተኞች ተዉላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
እንደገናም ልትቃርም ስትነሣ ቦዔዝ ጐልማሶቹን እንዲህ አላቸው፦ “በነዶዎች መካከል ያለውንም እንኳ ቢሆን ትቃርም፤ እናንተም አትከልክሉአት፤
አንድ ቀን ሞአባዊትዋ ሩት ናዖሚን “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው እርሻ ሄጄ ቃርሚያ ልቃርም” አለቻት። ናዖሚም “ልጄ ሆይ! ሂጂ!” አለቻት።
በዚህ ጊዜ ቦዔዝ ሩትን እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ! ስሚ እዚህ ያሉትን ሴቶች ሠራተኞችን ተከትለሽ ቃርሚ እንጂ ይህን እርሻ ትተሽ ለመቃረም ወደ ሌላ ቦታ አትሂጂ።