ስለዚህም ቅጣቱ በኢዮአብና በቤተሰቡ ላይ ይውረድ! በዘመናት ሁሉ ከቤተሰቡ የአባለ ዘር ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው አይጥፋ! እንዲሁም አካለ ስንኩል የሆነ ሰው፥ በጦር ሜዳ የሚሞት ወይም የሚበላው አጥቶ የሚራብ ሰው አይታጣ!”
ዘሌዋውያን 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው ከአባለ ዘሩ የሚወጣ ፈሳሽ ቢኖርበት፥ ያ ፈሳሽ ነገር ርኩስ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብላችሁ ንገሯቸው፤ ‘ማንም ሰው ከሰውነቱ ፈሳሽ ነገር ቢወጣ ያ ሰው ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ ማንም ሰው ከሰውነቱ ውስጥ ፈሳሽ ነገር ቢወጣ፥ ከእርሱ የሚወጣው ፈሳሽ ርኩስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ ከሰውነቱ ዘር የሚፈስሰው ሰው ቢኖር ስለሚፈስሰው ነገር ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ ማንም ሰው ከሥጋው ፈሳሽ ነገር ቢወጣ፥ ስለሚፈስሰው ነገር ርኩስ ነው። |
ስለዚህም ቅጣቱ በኢዮአብና በቤተሰቡ ላይ ይውረድ! በዘመናት ሁሉ ከቤተሰቡ የአባለ ዘር ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው አይጥፋ! እንዲሁም አካለ ስንኩል የሆነ ሰው፥ በጦር ሜዳ የሚሞት ወይም የሚበላው አጥቶ የሚራብ ሰው አይታጣ!”
“ከአሮን ተወላጆች ማንም ሰው የሥጋ ደዌ በሽታ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት ከሆነ እስከሚነጻበት ድረስ ከተቀደሰው ነገር አይብላ። በድን በመንካቱ የረከሰውን ነገር የሚነካ ወይም የዘር ፈሳሽ ያለበት
“አንድ ሰው ባለማወቅ ምንም ዐይነት ይሁን ከሰውነት የሚፈስ አንዳች ርኩስ ነገር ቢነካ፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል።
“የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበትን፥ ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውንና ሬሳ በመንካት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር ያወጡ ዘንድ እስራኤላውያንን እዘዝ፤
እነሆ፥ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት ትሠቃይ የነበረች አንዲት ሴት፥ በዚያን ጊዜ ከኢየሱስ በስተኋላ መጥታ የልብሱን ጫፍ በእጅዋ ነካች።
ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋም ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለሐኪሞች በመክፈል ጨርሳ ማንም ሊያድናት አልቻለም።