እንዲሁ እነርሱ በመቃብሮች መካከል የሚቀመጡ፥ በድብቅ ቦታዎች ሌሊቱን የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋ የሚበሉ፥ በዕቃቸውም ውስጥ የረከሰ ወጥ የሚያኖሩ ናቸው።
ዘሌዋውያን 14:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ የውስጡ ግድግዳ ሁሉ እንዲፋቅና ምርጊቱ ሁሉ ተቀርፎ ከከተማ ውጪ በሚገኘው በረከሰ ጒድፍ መጣያ እንዲጣል ያድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤቱ ግድግዳ በሙሉ በውስጥ በኩል እንዲፋቅና ፍቅፋቂው ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲደፋ ያድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቱንም ውስጥ ዙሪያውን ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቱንም በውስጡ በዙሪያው ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ወደ ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቱንም በውስጡ በዙሪያው ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ወደ ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል። |
እንዲሁ እነርሱ በመቃብሮች መካከል የሚቀመጡ፥ በድብቅ ቦታዎች ሌሊቱን የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋ የሚበሉ፥ በዕቃቸውም ውስጥ የረከሰ ወጥ የሚያኖሩ ናቸው።
የከተማሽን የቅጽር ግንቦች ያፈራርሳሉ፤ የዘብ መጠበቂያ ግንብሽን ይሰባብራሉ፤ ዐፈሩን ሁሉ ጠራርጌ በማጥፋት አለቱ ብቻ አግጥጦ እንዲቀር አደርጋለሁ፤
ኢየሱስ የገሊላን ባሕር ተሻግሮ፥ ወደ ጌርጌሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት የያዛቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ቦታ ወጥተው ተገናኙት፤ በጣምም አደገኞች ስለ ነበሩ ማንም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ አይችልም ነበር።
ከእነርሱ መካከል ሄሜኔዎስና እስክንድር ይገኛሉ፤ እነርሱ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ከመናገር መቈጠብን እንዲማሩ ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁ።
እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።