Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 14:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ቤቱ​ንም በው​ስጡ በዙ​ሪ​ያው ያስ​ፍ​ቀ​ዋል፤ የፋ​ቁ​ት​ንም የም​ር​ጊ​ቱን አፈር ከከ​ተ​ማው ወደ ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈ​ስ​ሱ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 የቤቱ ግድግዳ በሙሉ በውስጥ በኩል እንዲፋቅና ፍቅፋቂው ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲደፋ ያድርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 የቤቱንም ውስጥ ዙሪያውን ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ከዚያም በኋላ የውስጡ ግድግዳ ሁሉ እንዲፋቅና ምርጊቱ ሁሉ ተቀርፎ ከከተማ ውጪ በሚገኘው በረከሰ ጒድፍ መጣያ እንዲጣል ያድርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ቤቱንም በውስጡ በዙሪያው ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ወደ ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 14:41
10 Referencias Cruzadas  

ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።


ከእነዚያም እንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው።


ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


ወደ ማዶም ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተገናኙት፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ።


በመ​ቃ​ብ​ርም መካ​ከል የሚ​ተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚ​ያ​ልሙ፥ የእ​ሪያ ሥጋም የሚ​በሉ ናቸው። የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ደምና ዕቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያረ​ክ​ሳሉ።


እነ​ሆም፥ ደዌው በቤቱ ግንብ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድን​ጋ​ዮች እን​ዲ​ያ​ወጡ፥ ከከ​ተ​ማ​ውም ወደ ውጭ ወደ ረከ​ሰው ስፍራ እን​ዲ​ጥ​ሉ​አ​ቸው ያዝ​ዛል።


በእ​ነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች ስፍራ ሌሎች ድን​ጋ​ዮ​ችን ያገ​ባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስ​ደው ቤቱን ይመ​ር​ጉ​ታል።


ቤቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም፥ የቤ​ቱ​ንም ምር​ጊት ሁሉ ያፈ​ር​ሳል፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከከ​ተ​ማው ወደ ውጭ ወደ ርኩስ ስፍራ ያወ​ጣል።


የጢ​ሮ​ስ​ንም ቅጥ​ሮች ያፈ​ር​ሳሉ፤ ግን​ቦ​ች​ዋ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ፤ ትቢ​ያ​ዋ​ንም ከእ​ር​ስዋ እፍ​ቃ​ለሁ፤ እንደ ተራ​ቈተ ድን​ጋ​ይም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios