ዘሌዋውያን 14:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀኝ እጁ ጣት እያጠቀሰ ከዚያ ጥቂቱን በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም የቀኝ እጁን ጣት በመዳፉ በያዘው ዘይት ውስጥ በመንከር በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ጊዜ ይርጭ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም በግራ እጁ መዳፍ ላይ ያለውን ዘይት በቀኝ ጣቱ ሰባት ጊዜ በጌታ ፊት ይረጨዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም በግራ እጁ ውስጥ ከአለው ዘይት በቀኝ ጣቱ ሰባት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይረጨዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም በግራ እጁ ውስጥ ካለው ዘይት በቀኝ ጣቱ ሰባት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይረጨዋል። |
በእጁ ካለው ጥቂት ዘይት ወስዶ በበደል ስርየት መሥዋዕቱ ደም እንዳደረገው በሚነጻው ሰው በቀኝ ጆሮ የቀኝ እጁ አውራ ጣት መዳፍ ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ያስነካዋል።