ሰቈቃወ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፤ መተላለፊያዬንም አጣመመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዴን በተጠረቡ ድንጋዮች ዘጋ፤ ጐዳናዬንም አጣመመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዴን በዓለት ላይ ሠራ፤ ጎዳናዬንም አጠረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ። |
እስትንፋሱ እስከ አፍ ጢሙ ድረስ እንደ ሞላ ኀይለኛ የወንዝ ጐርፍ ነው። ሕዝቦችን በወንፊት እንደሚበጠር ብጣሪ አበጥሮ ያጠፋቸዋል። በመንጋጋቸውም ውስጥ የጥፋት ልጓም ለጒሞ ያጠፋቸዋል።
አምላክ ሆይ! ለምን መንገድህን እንድንስት አደረግኸን? እንዳንፈራህስ ለምን ልባችንን አደነደንክ? ለአገልጋዮችህ፥ የአንተ ስለ ሆኑት ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።