ሰቈቃወ 3:65 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርግማንህ በእነርሱ ላይ ይሁን! ተስፋ እንዲቈርጡም አድርጋቸው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልባቸው ላይ መጋረጃን ዘርጋ፤ ርግማንህም በላያቸው ይሁን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልብ ዕውርነትንና እርግማንህን ትሰጣቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልብ ሕማምንና ርግማንህን ስጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የልብ ዕውርነትንና እርግማንህን ትሰጣቸዋለህ። |
ቀጥሎም “እንዳያዩ፥ እንዳይሰሙና እንዳያስተውሉ በዓይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ ተመልሰው እንዳይፈወሱ ይህን ሕዝብ ልቡ የደነደነ፥ ጆሮው የተደፈነ፥ ዐይኑም የተጨፈነ እንዲሆን አድርግ” አለኝ።
“ነገር ግን ሲሖን ንጉሥ ሴዎን በእርሱ ግዛት ውስጥ አልፈን እንድንሄድ ባለመፍቀዱ፥ አሁን እንዳደረገው አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሊሰጠው ስለ ፈቀደ ትዕቢተኛና እልኸኛ አደረገው።