ሰው በወጣትነቱ መከራን በትዕግሥት ቢቀበል መልካም ነው።
ሰው በወጣትነቱ፣ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።
ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።
ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።
ሕግህን እንድማር ስላደረገኝ መቀጣቴ መልካም ሆነልኝ።
ጥበበኞች ለመሆን እንድንችል ዕድሜአችን ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስተምረን።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የምትገሥጸውና ሕግህንም የምታስተምረው ሰው እንዴት የተባረከ ነው!
በወጣትነትህ ዘመን ፈጣሪህን አስብ፤ ይህን ባታደርግ ግን ክፉ ቀን ይመጣብሃል፤ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመቶች ይደርሳሉ።
ሰው የእግዚአብሔርን አዳኝነት ጸጥ ብሎ መጠበቁ መልካም ነው።
እግዚአብሔር መከራውን በሚአመጣበት ጊዜ ጸጥ ብሎ ለብቻው ቢቀመጥ መልካም ነው።