ኢያሱ 9:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ጌታችን ሆይ! እኛ አገልጋዮችህ በእርግጥ ይህን አድርገናል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተ በውስጧ የሚኖሩትን ሕዝብ በመግደል ምድሪቱን ያወርሳችሁ ዘንድ አገልጋዩን ሙሴን ያዘዘው መሆኑን ዐውቀናል፤ ይህንንም ያደረግነው እናንተን ከመፍራታችን የተነሣ ሕይወታችንን ለማትረፍ ፈልገን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘው፣ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በርግጥ ለእኛ ለባሪያዎችህ ተነግሮናል፤ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይወታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልሰውም ኢያሱን እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ በእርሷም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ እንዲያጠፋ ጌታ አምላክህ ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፥ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ስለ ፈራን ይህን ነገር አድርገናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልሰውም ኢያሱን፥ “እኛ ባሪያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ ይሰጣችሁ ዘንድ፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ ያጠፋ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፤ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ፈራን፤ ይህንም ነገር አድርገናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልሰውም ኢያሱን፦ እኛ ባሪያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ ይሰጣችሁ ዘንድ፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ ያጠፋ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፥ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ፈራን፥ ይህንንም ነገር አድርገናል። |
ገባዖን በነገሥታት እንደሚተዳደሩት ከተሞች ትልቅና ከዐይ ትበልጥ የነበረች ከተማ ከመሆንዋም በላይ ሰዎችዋም ብርቱ ጦረኞች ስለ ነበሩ፥ አዶኒጼዴቅ በጣም ፈራ።
ስለዚህም ይህን ሁሉ ነገር በሰማን ጊዜ በፍርሃት ልባችን ቀለጠ፤ ወኔአችን ሁሉ ጠፋ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእርግጥ የሰማይና የምድር አምላክ ነው።
እንዲህ አለቻቸው፦ “የሀገሪቱ ኗሪዎች በሙሉ በፍርሃት ተውጠው ልባቸው ቀለጠ፤ በሁላችንም ላይ ፍርሀት ስላደረብን እግዚአብሔር ምድሪቱን ለእናንተ እንደ ሰጠ ዐውቃለሁ፤