ኢያሱ 5:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ሠራዊት አዛዥም “የቆምክባት ምድር የተቀደሰች ስለ ሆነች ጫማህን አውልቅ” አለው፤ ኢያሱም እርሱ እንዳዘዘው አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃም ኢያሱን፣ “ጫማህን ከእግርህ አውልቅ፤ የቆምህባት ምድር የተቀደሰች ናትና” አለው፤ ኢያሱም እንደ ታዘዘው አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ሠራዊት አዣዥ ኢያሱን፦ “አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፥ “አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፦ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ። |