እስከ ቤትሆግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜን በዮርዳኖስ ሸለቆ በኩል አልፎ የሮቤል ልጅ ወደ ሆነው ወደ ቦሐን መታሰቢያ ድንጋይ ድረስ ይወጣል።
ኢያሱ 18:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ወደ ሰሜን በመታጠፍ ወደ ዔንሺሜሽ አቅጣጫ ይሄዳል፤ ከዚያም ወደ ገሊሎት ይሄዳል፤ እርሱም ከአዱሚም ዐቀበት ትይዩ ነው፤ እንዲሁም የሮቤል ልጅ ወደ ሆነው ወደ ቦሄን ድንጋይ ይወርዳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ወደ ሰሜን ይታጠፍና በዓይንሳሚስ በኩል አድርጎ እስከ ጌሊሎት ይዘልቃል፤ ከዚያም በአዱሚም መተላለፊያ ትይዩ እስካለው እስከ ሮቤል ልጅ እስከ ቦሀን ድንጋይ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሰሜንም ታጥፎ በቤትሳሚስ ምንጭ ላይ ወጣ፥ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎት ደረሰ፤ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤተሳሚስም ምንጭ ያልፋል፤ በኢታሚም አቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ኬልዩት ይገባል፤ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቤዎን ድንጋይ ይወርዳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰሜንም አለፈ በቤትሳሚስ ምንጭ ላይ ወጣ፥ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎት ደረሰ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፥ |
እስከ ቤትሆግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜን በዮርዳኖስ ሸለቆ በኩል አልፎ የሮቤል ልጅ ወደ ሆነው ወደ ቦሐን መታሰቢያ ድንጋይ ድረስ ይወጣል።
ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ተነሥቶ ወደ ዳቢር ይወጣል፤ በሰሜን በኩልም አድርጎ ወደ ጌልጌላ ይመለሳል፤ እርሱ ከአዱሚም ትይዩ ይኸውም ከሸለቆው በደቡብ በኩል ነው፤ ስለዚህ ድንበሩ በኤንሼሜሽ ምንጭ በኩል ያልፋል፤ መጨረሻውም ኤን ሮጌል ነው።